Fana: At a Speed of Life!

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት 3 ሺህ 184 መጻሕፍት አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት 3 ሺህ 184 መጻሕፍት አበረከተ፡፡
የዩኒቨርሲቲው አብያተ መጻሕፍት ዳይሬክተር ወይዘሮ አዲስዓለም ጉልማ ÷ ትውልድን ለመቅረፅ ለተገነባው አብርሆት ቤተ መጻሕፍት የምናደርገውን ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ለአንድ ሣምንት የሚቆይ የመጻሕፍት አውደ ርዕይ ማዘጋጀቱን ገልጸው÷ በዓውደ ርዕዩ ላይ ዩኒቨርሲቲው ከተመሰረተ ጀምሮ በእጅ ተፅፈው የተሰነዱ የምርምር ሥራዎች እና ሌሎች ታሪካዊ መጻሕፍት ቀርበዋል ብለዋል፡፡
34 ሺህ 564 መጻሕፍት “ዲጂታላይዝ” ተደርገው የመማር ማስተማር ሂደቱን ማዘመን እንደቻሉም ወይዘሮ አዲስዓለም ተናግረዋል፡፡
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ወደ ምርምር ማዕከል ለሚያደርገው ጉዞ ስንቅ የሚሆነውን ዘመናዊ ቤተ መጻሕፍት እያደራጀ መሆኑም ገልጸዋል፡፡
በሁሴን ከማል
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.