Fana: At a Speed of Life!

ጆሴፍ ማጉፊሊ በታንዛኒያ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ከእስር ለመልቀቅ ወሰኑ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ማጉፊሊ በሀራቸው የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ክእስር ለመልቀቅ ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ጋር መስማማታቸውን ገለፁ።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ማጉፊሊ የሁለትዮሽ ውይይት ካደረጉ በኋላ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

ፕሬዚዳንቱ በህገ ወጥ መንገድ የታንዛኒያን ድንበር አቋርጠው የገቡ ኢትዮጵያወያን እስረኞች እንደሚገኙ በመግለፅ እስረኞችን ለመልቀቅ ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ጋር መወያየታቸውን ተናግረዋል።

በነፃ ከእስር ይፈታሉ ያሉት ፕሬዚዳንቱ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው በሀገራቸው ግንባታ ይሳተፋሉ ብለዋል።

ኢትዮጵያውያኑን ዛሬ ከፈለጉ ወደ ሀገራቸው መሄድ ይችላሉ ሲሉ የገለፁት ፕሬዚዳንቱ ከእስር ለሚለቀቁት የተቀመጠ ቅድመ ሁኔታ እንደሌለ ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወቅር ዘውዴ በበኩላቸው ከፕሬዚዳንት  ጆሴፍ ማጉፊሊ ጋር  በኢንቨስትመንት አመራጮች ዙሪያ መምከራቸውን ገልፀዋል።

የአፍሪካ መዲና እንደመሆኗ ስዋሂሊ ቋንቋን ለማስጀመር ፕሬዝዳንቱ ያቀረቡትን ሀሳብ ኢትዮጵያ እንደምታጤነው ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገልፀዋል፡፡
ከዚህ ባለፈ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ማጉፊሊ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ምርት ስኬታማነት ልምድ እንደምትወስድም ተናግረዋል።
ሁለቱ ሀገራት በቀጣይ ወራት የጋራ ኮሚሽን አቋቁመው በጋራ ጉዳዮች ላይ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውንም አስታውቀዋል፡፡

 

በኤፍሬም ምትኩ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.