Fana: At a Speed of Life!

ጉዳት የደረሰበትን የግብርና ዘርፍ በበጋ መስኖ ማካካስ ይገባል – የክልል ኢኮኖሚ ዘርፍ አስተባባሪዎች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2014(ኤፍ ቢሲ) በአሸባሪዎቹ ህወሓት እና ሸኔ ጉዳት የደረሰበትን የግብርና ዘርፍ በበጋ መስኖ ማካካስ እንደሚገባ የክልል ኢኮኖሚ ዘርፍ አስተባባሪዎች ገለፁ፡፡

ከፋና ቴሌቪዥን ስለ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ ያደረጉት በአማራ ክልል በርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የኢኮኖሚ ዘርፍ አስተባባሪ ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ እንደተናገሩት፥ አሸባሪዉ ህወሓት በክልሉ ግብርና ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡

በክልሉ ወረራ በፈጸመባቸዉ አካባቢዎች የግብርና ግበዓቶችን ዘርፏል፤ ፋብሪካዎች እና የሰብል ምርመር ተቋማትንም አዉድሟል ፡፡

በዚህም በክልሉ በአጠቃላይ 40 ሚሊየን ኩንታል ምርት ባክኗል ብለዋል ብለዋል ሃላፊዋ፡፡

ይህን የምርት ብክነት ለማካስም የበጋ መስኖ ልማት ላይ ማተኮር እንደሚገባ ሃላፊዋ አሳስበዋል፡፡

ይህን ተግባራዊ ለማድረግም በበጋ መስኖ 108 ሺህ ሄክታር ማሳ በበጋ መስኖ ለማልማት መታቀዱን ነው የገለፁት፡፡

አሁን ላይም አልሚ ባለሃብቶችን በማስተባበር በክልሉ ከወረራ ነፃ በሆኑ አካባቢዎች ከምርት መሰብሰብ ጎን ለጎን ለአየር ንብረት ሁኔታው ተስማሚ የሆኑ ምርቶችን ለማልመት እየተሰራ መሆኑን አብራረተዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል እርሻ እና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ አበራ ወርቁ በበኩላቸዉ ፥ በክልሉ 350 ሺህ ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ልማት ለመሸፈን እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የፍጆታ ምርቶችን ትኩረት ያደረገ የመስኖ ልማት በክልሉ እየተከናወነ መሆኑን የተናገሩት ሃላፊው፥ ይህም በክልሉ በድርቅ የተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎችን ለማቋቋም ይረዳል ነው ያሉት፡፡

በበጋ መስኖ ለመሸፈን የታቀደዉን ምርት ተግባራዊ ለማድረግም መንግስትና በዘርፉ ያሉ ድርጅቶች የበኩላቸዉን አስተዋፅኦ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.