Fana: At a Speed of Life!

ጋናዊቷ ሞዴል በኢትዮጵያ መልካም ህዝቦች የተደረገልኝ ሞቅ ያለ አቀባበል አስደንቆኛል አለች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጋናዊቷ ሞዴል ዶክተር ሴተር አብራ ኖርገቤ በኢትዮጵያ መልካም ህዝቦች የተደረገልኝ ሞቅ ያለ እና ደማቅ አቀባበል በጣም ድንቅ እና ያልጠበኩት ነበር ስትል ገለጸች።

ዶክተር ሴተር አብራ ኖርገቤ ÷ ጋና ኮቶካ አየር መንገድ ደርሼ ልዩ የሕክምና ምርመራ ከተደርገልኝ በኋላ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሳፍሬ ጉዞ እስክጀምር እና አዲስ አበባ እስክደርስ ድረስ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች ልዩ መስተንግዶ ቀርቦልኛል ብላለች፡፡

አዲስ አበባ ከደረስኩ በኋላ ደግሞ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስቴር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተቀብለውኛል ከፍተኛ የደኅንነት ጥበቃም አድርገውልኛል ስትልም ጋናዊቷ ሞዴል ገልጻለች፡፡

አዲስ አበባ በኢትዮጵያ ምግቦች ጣዕም እንደተደነቀች ገልጻ፥ ኢትዮጵያውያን ያሳዩዋት ፍቅር ልቧን እንደነካትም ጋናዊቷ አንስታለች፡፡

በመጨረሻም ኢትዮጵያ የኔ እና የቅድመ አያቶች ምርጥ የትውልድ ሀገር ናት ማለቷን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ጋናዊቷ ዶክተር ሴቶር ኖርግቤ በአገሯ ጋና በተካሄደው የቁንጅና ውድድር ኢትዮጵያ የሰው ዘር የበርካታ የቱሪስት መስህብ መገኛ መሆኗን አስተዋውቃለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.