Fana: At a Speed of Life!

የጋዜጠኛ እና አርቲስት ኢብራሂም ሀጂ አሊ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የጋዜጠኛ፣ አርቲስት እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ዕድገት ውስጥ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረከተው ኢብራሂም ሀጂ አሊ ስርአተ ቀብር ተፈጸመ፡፡

ኢብራሂም ሀጂ አሊ ካለፈው ክረምት ጀምሮ ባጋጠመው የጤና እክል ሳቢያ የህክምና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቶ ትናንት ሌሊት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል፡፡

የቀብር ስነስርዓቱም ዛሬ 9፡00 ሰዓት ላይ ቤተሰቦቹ፣ የስራ ባልደረቦቹ የሙያ አጋሮቹ እንዲሁም አድናቂዎቹ በተገኙበት በኮልፌ የሙስሊም መቃብር ተፈጽሟል፡፡

ጋዜጠኛ፣ አርቲስት እና የቋንቋ ተመራማሪው በሙዚቃ ህይወቱ በርካታ ነጠላ ዜማዎችን ያበረከተ ሲሆን፣ አራት ዓይነት የሙዚቃ መሳሪያዎችን መጫወት ይችል ነበር፡፡

ኢብራሂም ሀጂ አሊ ሙዚቃን የጀመረው ተወልዶ ባደገበት በድሬዳዋ ሲሆን በ1967/68 የአርፈን ቀሎ ባንድ 2ኛ ትውልድ በመባል በሚጠራው ከአዱ ቢራ ባንድ መስራቾች ከሚባሉት የክብር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ፣ ሂሜ የሱፍ፣ አብዱ ሸኩር፣ መሀመድ ጠዊል ጋር በመሆን አንደኛው መስራች ነበረ፡፡

ከዚያን ጊዜ በኋላ የጋዜጠኝነት ህይወትን እስከሚቀላቀል የአፋን ኦሮሞ ሙዚቃን በኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢዎች ለማስተዋወቅ እድል አግኝቶ ተጠቅሞበታል፡፡

በ1968 ዓ.ም በሪሳ ጋዜጣ ስራ ሲጀምሩ ኢብራሂም ሀጂ አሊ አንደኛው ጋዜጠኛ ነበረ፡፡

ኢብራሂም የግጥም እና ዜማ ደራሲ እንደነበረም በቅርብ የሚያውቁት እና የእርሱን ስራዎች የተጫወቱ ይመሰክሩለታል፡፡

በ1987 ዓ.ም ሬዲዮ ፋና ሲመሰረት ፋናን ከተቀላቀሉ አንጋፋ ጋዜጠኞች መካከልም አንደኛው ሲሆን ተወዳጅ የሆነውን ፋና አፋን ኦሮሞ ፕሮግራምን አዘጋጅቶ በማቅረብም ይታወቃል፡፡

ኢብራሂም በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እስከ ኤዲተርነት ያገለገለ ሲሆን ህይወቱ እስከሚያልፍ ድረስም የስፖርት ጋዜጠኛ ነበር፡፡

አፋን ኦሮሞ በጥናት ላይ ተመስርቶ እንዲያድግም ጥረት ካደረጉ ታላላቅ ሰዎች መካከል አንደኛው መሆኑ ይነገራል፡፡

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.