Fana: At a Speed of Life!

ግለሰቡ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን ለሰራዊቱ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁስ አበረከቱ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ ተስፋሁን ደረጃ በውጪ ከሚኖሩ ቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን 200 ሺህ ብር የሚገመቱ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁስ በግንባር ለሚፋለመው ሰራዊት አበረከቱ።
በአዲስ አበባ የሚኖሩት ግለሰቡ ድጋፉን ያበረከቱት ጎንደር ከተማ በመገኘት ነው።

የአገርን ህልውና ለማስጠበቅ መንግስት ህዝቡና ሰራዊቱ እያደረጉት ያለውን ተጋድሎና ርብርብ አቅም በፈቀደ መጠን መደገፍ የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ግዴታው ነው ብለዋል አቶ ተስፋሁን በሰጡት አስተያየት።

አገር የሁሉም ዜጎቿ መኖሪያና መከበሪያ በመሆኗ ሉአላዊነትና ነጻነት ቅድሚያ በመስጠት የቤተሰብ አባላቱ በግንባር ለሚዋደቀው የፀጥታ ሃይል ድጋፉን ማበርከታቸውን ተናግረዋል።

ከድጋፉ መካከል ለሰራዊቱ የውሃ መያዣ የሚውሉ ኮዳዎች፣ እሽግ ውሃ፣ አልባሳት፣ ጫማዎች፣ የለስላሳ መጠጦችና ቴምር ይገኙበታል።

በቀጣይም ሰራዊቱ የሽብር ቡድኑን ደምስሶ ለኢትዮጵያ ህዝብ ድል እስከሚያበስር ድረስ ድጋፋቸውን አጠናክረው ለመቀጠል ቃል መግባታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደ፥ የቤተሰብ አባላቱ ያደረጉትን ድጋፍ በደባርቅ ግንባር ለሚገኘው የጸጥታ አካል በፍጥነት እንዲደርስ እንደሚደረግም አስታውቀዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.