Fana: At a Speed of Life!

ግምታቸው ከ9 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የኮንትሮባንድ ሲጋራዎችና ልባሽ ጨርቆች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሸዋ ዞን መተሓራ ከተማ ግምታቸው ከ9 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የኮንትሮባንድ ሲጋራዎችና ልባሽ ጨርቆች መያዛቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ዲቭዥን ሃላፊ ኮማንደር አስቻለው ዓለሙ ለኢዜአ እንደገለጹት የኮንትሮባንድ ሲጋራዎችና ልባሽ ጨርቆቹ ከአዋሽ ሰባት ወደ አዳማ በመጓጓዝ ላይ እንዳሉ ትናንት እኩለ ለሊት ላይ በፀጥታ ሃይሎች ክትትል ተይዘዋል።

የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 29477 ኢ.ት በሆነ ተሽከርካሪ ተጭነው በመጓጓዝ ላይ እንዳሉ መያዛቸውን ተናግረዋል።

በመተሓራ ከተማ ጸጥታ አካላት ክትትል የተያዙት 11ሺህ 299 ስቴካ ሸምለን፣ጎልደንና ሮያል የተሰኙ ሲጋራዎን ጨምሮ 120 ቦንዳ ልባሽ ጨርቆች መሆናቸውን ኮማንደር አስቻለውን ጠቅሰዋል።

የተያዙት ሲጋራዎችና ልባሽ ጨርቆች ከ9 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው መሆኑን የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።

የከተማዋ የፀጥታ አካላትና ነዋሪው የአካባቢውን ሰላም ከመጠበቅ ባለፈ ህገ ወጥ ንግድና የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን በመከላከል ረገድ ቁልፍ ሚና እየተወጡ መሆኑን ሃላፊው አመልክቷል።

የተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች በኢትዮጵያ ጉሙሩክ ኮሚሽን ለአዋሽ ሰባት የጉሙሩክ ቅርንጫፍ ገቢ መደረጉን ኮማንደር አስቻለው አስታውቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.