Fana: At a Speed of Life!

ግብርናችንን በማዘመን እራሳችንን መቻል ወሳኝ ነው – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጪ ተጽዕኖን ለመቋቋም ግብርናችንን በማዘመን በምጣኔ ሀብት እራሳችንን መቻል ወሳኝ ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፡፡
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ በኦሮሚያ ክልል የግብርና ስራዎችን እየጎበኘ ነው።
ግብርናን ለማዘመን በኦሮሚያ ክልል የተሰራውን ሥራ እንደ ሀገር በማስፋፋት ታሪክ መስራት ይቻላል ብለዋል አቶ ደመቀ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን፣ የኦሮሚያ ክልል ርእስ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የሚኒስትሮች ልዑካን ቡድን በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳሚ ቱሉ ጂዶ ኮምቦልቻ ወረዳ በኩታ ገጠም የለማ የስንዴ እና የበቆሎ ማሳ ጎብኝተዋል ሲል ኦ ቢ ኤን ዘግቧል፡፡

ልዑካን ቡድኑ ረፋድ ላይ  በምስራቅ ሸዋ ዞን አደኣ ወረዳ በኩታ ገጠም የለሙ እህሎች፣ አትክልት እና ፍራፍሬዎችን  መጎብኘቱ ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.