Fana: At a Speed of Life!

ግብርና ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ የማቅረቡ ስራ እንደቀጠለ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ሽንኩርትና ሌሎች የግብርና ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለሕብረተሰቡ የማቅረቡ ስራ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ጊዜያት በግብርና እና ኢንዱስትሪ ምርቶች ላይ የሚስተዋለውን ሰው ሰራሽ የዋጋ ንረት ለመከላከል እና የተቀጣጠለውን የደላላ ሰንሰለት በመበጣጠስ ህብረተሰቡ እነዚህን ምርቶች በቀጥታ እንዲያገኝ የከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
የግብርና ምርት አቅርቦት እና ፍላጎት እንዲሁም ተያያዥ ችግርን ለመቅረፍም የከተማ አስተዳደሩ ከኦሮሚያ እና ሌሎች የክልል አርሶ አደሮች ጋር ውል በመግባት የሽንኩርት እና ሌሎች የግብርና ምርቶችን ቀጥታ ህብረተሰቡ ጋር እንዲደርስ እየተደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በዛሬው እለትም ከ531 ኩንታል በላይ ቀይ ሽንኩርት ከኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ወደ ከተማዋ በማስገባት በሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት በኩል ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የማከፋፈል ስራ ተሰርቷል፡፡
በከተማዋ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት ሱቆች እና በተመረጡ ከ19 በላይ ዋና ዋና ጎዳናዎች፥ ከ1ሺህ 500 ኩንታል በላይ ቀይ ሽንኩረት እና ሌሎች የግብርና ምርቶች ለህብረተሰቡ ስርጭት እንደተካሄደ የከተማዋ ህብረት ሥራ ኤጀንሲ ገልጿል፡፡
በቀጣይም በማህበራቱ በኩል ሌሎች የግብርና ምርቶች በቀጥታ ከአምራች የህብረት ስራ ማህበራት ጋር የገበያ ትስስር በመፍጠር የኑሮ ውድነቱን የማቃለል ስራ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
0
People reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.