Fana: At a Speed of Life!

ግብፅ ቱርክ ወታደሮቿን ወደ ሊቢያ ለመላክ ያሳላፈችውን ውሳኔ አወገዘች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ግብፅ የቱርክ ፓርላማ የሀገሪቱ ወታደሮች ወደ ሊቢያ እንደሚያመሩ ያሳላፈውን ውሳኔ እንደምታወግዝ ገለጸች።

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የቱርክ ወታደሮችን መላክ የሜዲትራንያንን አካባቢ መረጋጋት በእጅጉ የሚጎዳ በመሆኑ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል።

የቱርክ ፓርላማ በትናንትናው ዕለት 352 ለ 184 በሆነ ድምፅ የሀገሪቱ ወታደሮች የፋይዝ ሳራጅን አስተዳደር ለመደገፍ ወደ ሊቢያ እንዲያቀኑ ውሳኔ አሳልፏል።

ይህ ውሳኔ የቱርክ መንግስት ወታደሮቹን ለአንድ ዓመት ወደ ሊቢያ እንዲልክ አረንጓዴ መብራት ያበራ ነው ተብሏል።

ሊቢያ ሙዐመር ጋዳፊን ከስልጣን ካወረደች ከፈረንጆቹ 2011 ጀምሮ በእርስ በርስ ጦርነት እየታመሰች ትገኛለች።

በጄኔራል ሃፍታር የሚመራው አስተዳደር ትሪፓሊን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር እያደረገ ያለው ጦርነት መባባሱ ተጠቁሟል።

ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲ ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.