Fana: At a Speed of Life!

ግብፅ ከምትፈፅመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ እርምጃ እንዲወሰድባት ውሳኔ ሀሳብ በአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ፀደቀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ፓርላማ አባል ሀገራቱ ግብፅ እየፈፀመችው ከሚገኘው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ እርምጃ እንዲወስዱ የውሳኔ ሀሳብ አሳለፈ።

የአውሮፓ ፖለቲከኞች ግብፅ በምትፈፅመው የሰብዓዊ መብት ምክንያት ቆራጥ እና የተቀናጀ እርምጃ ሊወሰድባት ይገባል ሲሉ አፅዕኖት ሰጥተዋል።

የሁሉንም መሳሪያዎች በመቀጠም የግብፅ መንግስት እየፈፀመ የሚገኘውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ማስቆም ይገባል ብለዋል።

ውሳኔ ሀሳቡ 434 የድጋፍ ድምፅ ፣ በ49 ተቃውሞ እና በ202 ድምፅ ተዓቅቦ የተፀደቀ ሲሆን የአውሮፓ ህብረት ከግብፅ ያለው ግንኙነት በጥልቅ ሊገመገም እንደሚገባ መነገሩን አልጀዚራ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.