Fana: At a Speed of Life!

እስከ ታችኛው መዋቅር ያለውን አሰራር በመቀየር ገፊ የኢንቨስትመንት አሰራር ማነቆዎችን ማሻሻል ይገባል – የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ከክልሉ መንግስት ጀምሮ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ያለውን አሰራር በመቀየር ገፊ የሆኑ የኢንቨስትመንት አሰራር ማነቆዎችን ማሻሻል እንደሚገባ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ ተናገሩ፡፡

ጎንደር ከተማና አካባቢውን ከኢንቨስትመንት ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ምክክር ተደርጓል፡፡

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ከተማዋ ለሕዝቧና ለታሪኳ የሚመጥን የልማት ሥራ ሳይሠራባት ቆይቷል ብለዋል፡፡

በዘርፉ የነበሩ ክፍተቶችን ለመሙላት እርስ በርስ ከመወቃቀስ ያለፉ ሥራዎች እንዲሠሩም አሳስበዋል፡፡

አያይዘውም ከተማዋ ከኢንቨስትመንት ተጠቃሚ እንድትሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚገባቸውን ሊሠሩ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

ባለሃብቱም ቢሆን የወሰደውን መሬት በአግባቡ በመጠቀም ወደ ልማት መቀየር ይኖርበታልም ነው ያሉት፡፡

ህብረተሰቡም የሚያነሳቸውን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ በየትኛውም ሁኔታ አስፈላጊ የሚባሉ ትብብሮችን ሊያደርግ ይገባልም ነው ያሉት፡፡

መንግስትም ለልማት የሚነሱ ዜጎችን ካሳ ከመክፈል ባለፈ ልማቱ ላይ ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚሆኑበትን እድል እንደሚያመቻች ጠቅሰው፥ በቅንጅት በመስራት ባለሃብቶች የከተማዋን ብሎም የሃገሪቱን የምግብ ዋስትና እና የኢንቨስትመንት መስፋፋትን ማረጋጋጥ ይችላሉም ብለዋል፡፡

የጎንደር ከተማ አስተዳደር በዘንደሮው አመት ከ490 ሄክታር በላይ ለኢንቨስትመንት የሚሆን መሬት አዘጋጅቷል፡፡

የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ የመጡ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የከተማዋ ተወላጆች በምክክር መድረኩ ላይ የተሳተፉ ሲሆን፤ ለዘርፉ ማነቆ የሆኑ ተግዳሮቶች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በዘቢብ ተክላይ እና ዮርዳኖስ አበበ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.