Fana: At a Speed of Life!

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለፀጥታ ኃይሎች እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠሉን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሀገር በማስከበር ላይ ለሚገኙት የፀጥታ ኃይሎች እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው፥ 972 ሺህ 600 ብር የሚገመት 209 ኩንታል ኩኪስና 20 ኩንታል ተምር በዋግኽምራ ዞን ሰቆጣ ግንባር እና በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንድውሃ ለሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች የሚውል ደረቅ ሬሽን አስረክቧል።
በርክክብ ሥነሥርዓቱ ላይ የዞንና የወረዳ ኃላፊዎችና የሎጅስቲክስ አስተባባሪዎች መገኘታቸውን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በተለያየ ጊዜ የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብሰብ ሰፊ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.