Fana: At a Speed of Life!

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በማይካድራ ጭፍጨፋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩኒቨርሲቲው ከ265 ሺህ ብር በላይ ወጭ በማድረግ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ተጎጅዎችና ለሟች ቤተሰቦች የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
ዩኒቨርሲቲው ተጎጂ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም ማቀዱን ገልጾ÷ በአሁኑ ጊዜ ግን በአፋጣኝ በዕለት ደራሽ ምግቦች ማገዝ አስፈላጊ በመሆኑ 32 ኩንታል ጤፍ፣ 32 ካርቶን ፓስታ፣ 2ዐዐ ኪሎ ስኳር፣ 1ዐዐ ኪሎ በርበሬ፣ 3 ኩንታል ጨው እንዲሁም 160 ሊትር ዘይት በጠቅላላ ግምቱ 265 ሺህ 200 ብር የሚተመን ድጋፍ አድርጓል፡፡
በድጋፉም÷ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ተጎጂዎች እንዲሁም የሟች ቤተሰቦች ተደራሽ ሆነዋል፡፡
ማይካድራ ከተማ በመገኘት የድጋፍ ርክክቡን ያካሄዱት የጎንደር ዩኒቨርስቲ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጋሻው አንዳርጌ እና የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተሩ አቶ ሰሎሞን ፋንታው መሆናቸውን ከዩኒቨርሲቲው የማኅበራዊ ሚዲያ ትሥሥር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.