Fana: At a Speed of Life!

ጎግልን ጨምሮ ስመ ጥር የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ተቋማዊ የዘር መድሎ ይፈጽማሉ- ትምኒት ገብሩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ”አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ” ተመራማሪ ዶክተር ትምኒት ገብሩ ሰሞኑን ከጎግል ኩባንያ ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባቷ የትኩረት ማዕከል አድርጓታል።

ዶክተር ትምኒት ባዘጋጀችው የጥናት ወረቀት እና ጎግል ሰራተኞችን በተለይም ከፆታ እና ከቀለም ጋር ተያይዞ የሚያስተናግድበትን መንገድ በተመለከተ ከተቸች በኋላ ተቋሙን እንድትለቅ መገደዷ የሚታወስ ነው።

ይህን ተከትሎም የጎግል ሰራተኞችም ሆኑ ሌሎች አካላት የጎግልን እርምጃ በመቃወም የተለያዩ አስተያየቶችን ሲሰጡ ቆይተዋል።

ጫና የበዛበት የሚመስለው የጎግል ዋና ስራ አስፈፃሚ ሰንዳር ፒቻይም የ”አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ” ተመራማሪዋ ዶክተር ትምኒት ገብሩ ተቋሙን ስለለቀቀችበት መንገድ ይቅርታ በመጠየቅ ጉዳዮ እንደሚጣራ ገልፀዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ዶክተር ትምኒት ጎግልን የለቀቀችበትን ሁኔታ እንገመግማለን ያሉ ቢሆንም ተቋሙ አሰናብቷታል ብለው ለመናገር አልደፈሩም ብሏል ቢቢሲ በዘገባው።

ዶክተር ትምኒት እና ደጋፊዎቿ ከጎግል በተሰናበትችበት ሁኔታ ተቋማዊ የዘር መድሎው ትልቅ ሚና መጫወቱን እንደሚያምኑ ይናገራሉ።

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ በዘርፉ ካሉ ውስን ጥቁር ሴት ባለሙያዎች መካከል አንደኛዋ መሆኗ ይነገራል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ለቢቢሲ እንደተናገረችው በቴክኖሎጂው ዘርፍ የጥቁር ሴቶች ተሳትፎ ዝቅ ያለው በድንገት አይደለም ብላለች።
በመሆኑም ጎግል እና ሌሎች የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ተቋማዊ የዘር መድሎ ይፈፅማሉ ስትል ነው የተናገረችው።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.