Fana: At a Speed of Life!

ጎግል ሰራተኞቹ ቤት ውስጥ ሆነው እንዲሰሩ ጠየቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 2 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ጎግል በዓለም ላይ በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ሰራተኞቹ ቤት ውስጥ ሆነው እንዲሰሩ ጠይቋል።

የጎግል እህት ኩባንያ የሆነው አልፋ ቤት ሰራተኞቹ ስራቸውን ቤት ውስጥ እንዲከውኑ ጠይቋል፤ ጥያቄው በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ሰራተኞችን የሚመለከት ነው ተብሏል።

ጎግል ከሳምንት በፊት ሰራተኞቹ ቤት ውስጥ ሆነው ቢሰሩ የተሻለ ነው የሚል ምክረ ሃሳብ አቅርቦ ነበር።

አሁን ላይ የቀረበው ጥያቄ በአሜሪካ እና ካናዳ በ11 ቢሮወቹ የሚገኙ 100 ሺህ ሰራተኞችን የሚመለከት ነው።

በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰወች ቁጥር ወደ 1 ሺህ ደርሷል፥ ከዚህ ጋር ተያይዞም ጎግልን ጨምሮ አፕል፣ አማዞን፣ ማይክሮሶፍት እና ፌስቡክ ሰራተኞቻቸው ስራቸውን ቤት ውስጥ ቢያከናውኑ የተሻለ ነው የሚል ምክረ ሃሳብ አቅርበዋል።

ሆኖም አልፋቤት የሰሜን አሜሪካ ቢሮው ስራቸውን ቢሮ ውስጥ ሆነው ለሚሰሩ ሰራተኞቹ ክፍት መሆኑ ገልጿል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.