Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትሩ  በትግራይ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች  216 ሺህ ብር አበረከቱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች  እገዛ እንዲውል  216 ሺህ ብር ትናንት አበረከቱ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገንዘቡን ያበረከቱት ከመፀሐፋቸው ሽያጭና የወር ደመወዛቸው በመቀነስ እንደሆነ ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪም  ሶስት የውሃ ማመላለሻ ተሽከርካሪ  ቦቴዎችን በማመቻቸት ለጊዜያዊ አስተዳደሩ እንዲደርስ አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩን በመወከል ድጋፉን  ያስረከቡት የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች  ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ እቴነሽ ንጉሴ ናቸው።

ድጋፉን የተረከቡት የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እቅድና ፋይናንስ ቢሮ አስተባባሪ  አቶ ካህሳይ ብርሃኑ እንደገለጹት  ጠቅላይ ሚኒስትሩ በገቡት  ቃል መሰረት ከመጽሐፋቸው ሽያጭ 200 ሺህ ብር እና ከወር ደመወዛቸው ደግሞ  16 ሺህ ብር አበርክተዋል።

በክልሉ  የተቸገሩ ወገኖችን ለመርዳት አሁንም ድጋፍ ስለሚያስፈልግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አርአያነት በመከተል ሌሎችም  እጃቸውን እንዲዘረጉ ጠይቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቅርቡ ስለትግራይ መልሶ ግንባታ ከክልል ፕሬዚዳንቶችና ከተማ አስተዳደሮች ጋር በበይነ መረብ መመክራቸውን፤ ለዚህም የአንድነት ተግባር ከወር ደመወዛቸውና ከመደመር መጽሐፋቸው ሽያጭ ገንንዘብ እንዲሁም በጽህፈት ቤታቸው  በኩል ሶስት የውሃ ማመላለሻ ተሽከርካሪ  ቦቴዎችን ማዋጣታቸውን በወቅቱ ይፋ አደርገዋል።

በዚህ ወቅትም ሁሉም ሰው ትግራይን መልሶ በመገንባቱ የአንድነት ንቅናቄ እንዲሳተፍ ጥሪ  ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.