Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለጥበብ ባለሙያዎች እውቅና ሰጡ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ‘ቢይ አሕመድ በእንጦጦ ፓርክ ለኢትዮጵያ የጥበብ ባለሙያዎች እውቅና ሰጡ፡፡

“ኢትዮጵያን ስላገለገላችሁ ኢትዮጵያ ታመሰግናችኋለች” በሚል ሀሳብ ነው እውቅናው የተሰጠ።

በመርሃ ግብሩ በሁሉም የጥበብ ዘርፍ ለሃገራቸው ውለታ የዋሉ የጥበብ ሰዎች ተገኝተዋል።

አንጋፋ የኪነጥበብ ባለሙያዎችም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እጅ የእውቅና ሜዳልያ ተበርክቶላቸዋል።

የተሸላሚ አርቲስቶች መረጣ የተከናወነው በኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ውስጥ ባበረከቱት አስተዋጽኦ፣ ሀገራቸውን በንቃት ማገልገላቸው፣ የተቀባይነት መጠን፣ ለሙያቸው እድገት ያበረከቱት አስተዋጽኦ፣ እድሜያቸው ወደ ስልሳዎቹ የተጠጋና ከዚያ በላይ የሆነ እንዲሁም በህይወት ያሉ ናቸው።

በቴአትር ፣ በፊልም፣ በስዕል እና ኪነቅርጽ የተሰማሩ ባለሙያዎች ተሸልመዋል፡፡

በዓላዛር ታደለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.