Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሀዋሳ በግንባታ ላይ ያለውን የዳቦ ፋብሪካ ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሀዋሳ በግንባታ ላይ የሚገኘውን የዳቦ ፋብሪካ የግንባታ ሂደት ጎበኙ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና በእርሳቸው የተመራው ልዑክ በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት እየተገነባ ያለውን የዳቦ ፋብሪካ የግንባታ ሂደት ጎብኝቷል፡፡
የዳቦ ፋብሪካው በቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት ስር በሀገር ደረጃ ከሚገነቡ 10 የዳቦና የዱቄት ፋብሪካዎች አንዱ ተብሏል፡፡
የፋብሪካው ግንባታ በፍጥነት ተሰርቶ እንዲጠናቀቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትዕዛዝ መስጠታቸው ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም÷ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በክልሉ እየተሰሩ ያሉ ሌሎች የልማት ስራዎችን እየጎበኙ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ትናንት የወላይታ ሶዶ ከተማ አውሮፕላን ማረፊያ እና የዳቦና የዱቄት ፋብሪካ የግንባታ ሂደት መጎብኘታቸው የሚታወስ ሲሆን ÷ትናንት ማምሻውን ሀዋሳ ከተማ ገብተዋል።
በታሪኩ ለገሰ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.