Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሰብል ስብሰባ ለተሰማሩ  ተማሪዎችና  መምህራን  አድናቆታቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተያዘው ሳምንት በሰብል ስብሰባ ለተሰማሩ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችና አስተማሪዎች  ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ  በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ በተያዘው ሳምንት  የአርሶ አደሮችን የደረሱ ሰብሎች ለመሰብሰብ በተለያዩ አካባቢዎች የተሰማሩ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችን እና መምህራንን አድንቀዋል፡፡

እንደ ሀገር በአንድነት ሆነን በጽናት ጉዟችንን እንቀጥላለንም ነው ያሉት፡፡

የትምህርት ማህበረሰቡ ለህልውና ዘመቻው ደጀን እንዲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ከህዳር 27 እስከ ታህሳስ 3 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ዝግ እንዲሆን ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ ይታወሳል።

በውሰኔው መሰረትም ትምህርት ዝግ በሚሆንበት ሳምንት መምህራንና ተማሪዎች አገርን በጋራ ለማቆም በሚደረገው ትግል ውስጥ የትምህርት ማህበረሰቡ ተሳትፎ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተመልክቷል።

የትምህርት ማህበረሰቡ በሰብል መሰብሰብና በስንቅ ዝግጅት እንደሚሳተፍም ነው የተጠቆመው።

ይህንኑ ተከትሎ በአዲስ አበባ የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ለሚሰበስቡ 30 ሺህ የትምህርት ማህበረሰብ አባላት ዛሬ ሽኝት ተደርጎላቸዋል ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.