Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፈረንሳይ ምርጫ በድጋሚ ላሸነፉት ፕሬዚዳንት ማክሮን የደስታ መግለጫ አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፈረንሳይ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በድጋሚ ላሸነፉት ኢማኑኤል ማክሮን የደስታ መግለጫ አስተላለፉ።

በሀገሪቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዛሬ በተሰጠ የመጨረሻ ዙር ድምፅ በስልጣን ላይ ያሉት ማክሮን ተፎካካሪያቸውን ማሪን ሌፔንን አሸንፈዋል።

ይህንን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ባስተላለፉት የደስታ መግለጫ፥ ማክሮንን “ለስኬታማውና ታሪካዊ ዳግም ምርጫ እንኳን ደስ ያልዎት” ብለዋል።

የሁለቱን ሀገራት ጠንካራ ግንኙነት ለማስቀጠል በቀጣይ በጋራ እንደሚሠሩ ነው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባወጡት መልዕክት የገለፁት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.