Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን የሚደግፍ ሰልፍ በኮንሶ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮንሶ ዞን ነዋሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና እየተመዘገበ ላለው ለውጥ አጋርነታችን የሚያሳይ የድጋፍ ሠልፍ አካሄዱ።

በኮንሶ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እየሰጡት ያለውን የለውጥ አመራርና ስኬቱን በማድነቅ ከጎናቸው መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የድጋፍ ሰልፍ በካራት ከተማ አካሂደዋል።

ሠልፈኞቹ ‘ታላቁ የለውጥ ጉዟችን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መሪነት ይጠናከራል፣ በኮንሶ ዞን ሠገን ዙሪያ ወረዳ ሠላም የሚያደፈርሱ ፀረ ሠላም ኃይሎችን በህዝባችን ትብብርና አንድነት የቀጠናውን ሠላም እናረጋግጣለን፣ ከብልጽግና ጋር ስኬታማ እንሆናለን፣ ለውጡን የሚያደናቅፍ የሴራ ፖለቲካ እናወግዛለን የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።

በተጨማሪም ፈተናዎችን እያመከንን የለውጡን ዘላቂነት እናረጋግጣለን፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን የሚያደናቅፍ የውስጥና የውጭ ኃይሎችን እናወግዛለን፣ በጁንታው መቃብር ላይ ብልጽግና ይረጋገጣል፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የጁንታውን ቡድን ለማምከን የሰጡትን በሳል አመራር እናደንቃለን ፣ ሠላምና የሕዝቦች አንድነት ይለመልማል’ የሚሉና ሌሎችንም መልዕክቶች አስተላልፈዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.