Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
በተለይም በሀገራዊና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው መምከራቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከዚህ ባለፈም ሁለቱ ሀገራት በባህል ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ ለማሻሻል እና በቀጣይም በአዳዲስ ዘርፎች በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
የጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ትናንት ምሽት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።
ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በሚኖራቸው የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.