Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሱዳኑ አቻቸው አብደላ ሓምዶክና ከሶማሊያው ፕሬዚዳንት ጋር የተናጠል ውይይት አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 11፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከሱዳኑ አቻቸው አብደላ ሓምዶክና ከሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሀመድ ፋርማጆ ጋር የተናጠል ውይይት አካሄዱ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ  ከሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሓምዶክ ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል።

መሪዎቹ በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።

መሪዎቹ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከርና አካባቢያዊ ትስስርን ማጎልበት ላይ ተወያይተዋል።

በተመሳሳይ  ከፕሬዚዳንት መሀመድ ፋርማጆ ጋር የኢጋድ አባል ሀገራትን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር መሰራት እንዳለበት መወያየታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትዊተር ገጿቸው ገልጸዋል።

እንዲሁም  ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ከ38ኛ የኢጋድ አስቸኳይ የመሪዎች ስብሰባ ጎን ለጎን የሁለትዮሽ ውይይት አካሄደዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጣናዊ እና በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ከፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር መምከራቸውን ገልፀዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ያካተተ የልኡካን ቡድን ወደ ስፍራው አቅንቷል።

ጉባኤው በአፍሪካ ቀንድ የሰላምና ፀጥታ እንዲሁም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዙሪያ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.