Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በታዋቂው የኦሮሚኛ ቋንቋ ሙዚቀኛ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በታዋቂው የኦሮሚኛ ቋንቋ ሙዚቀኛ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀዘን መግለጫቸው “ውድ ህይወት አጥተናል” ብለዋል።

“የዚህ ድንቅና አንፀባራቂ ወጣት አርቲስት ሓጫሉ ሁንዴሳ ህይወት መቀጠፍ ከተሰማ ጀምሮ በከባድ ሀዘን ውስጥ ለምንገኝ ሁሉ መፅናናትን እመኛለሁም” ነው ያሉት ።

የዚህን ክፉ ድርጊት ሙሉ የፖሊስ ምርመራ ሪፖርት እየተጠባበቅን እንገኛለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የድርጊቱን መጠን በመረዳት በሀገራችን ውስጥ ስለሚከናወኑ እንቅስቃሴዎች ትኩረት ሰጥተን የምንከታተልበት ወቅት ላይ እንገኛለን ብለዋል።

ሀዘናችንን ራሳችንን በመጠበቅ እና ተጨማሪ ወንጀልን በመከላከል እንግለፅ ሲሉም አሳስበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.