Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ ሰላትን በየቤቱ እንዲሰግድ አሳሰበ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ ሰላትን በየቤቱ መስገድ እንዳለበት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳሰበ።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር እንድሪስ 1 ሺህ 441ኛውን የኢድ አል ፈጥር በዓልን በማስመልከት መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም ህዝበ ሙስሊሙ የዘንድሮውን የኢድ በዓል ሲያከብር የኮሮና ቫይረስ የተከሰተበት ወቅት በመሆኑ ቫይረሱ እንዳይሰራጭ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል ነው ያሉት።

በመሆኑም ሁሉም የኢድ ሰላትን በየቤታቸው ሆነው እንዲሰግዱ አሳስበዋል።

በዓሉ ሲከበርም የተቸገሩትን በመርዳት፣ በመተጋገዝና በመተዛዘን እንዲሁም አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ መሆን እንደሚገባውም ተናግረዋል።

1 ሺህ 441ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ዛሬ ምሽት ጨረቃ ከታየች ነገ ቅዳሜ ዛሬ ካልታየች ደግሞ እሁድ ተከብሮ የሚውል መሆኑንም ገልጸዋል።

የዘንድሮው የኢድ በዓል የሚከበረው መንግስት ለህዝበ ሙስሊሙ በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ መስጂድና ኢስላማዊ ማዕከል የመስሪያ ቦታ ባስረከበ ማግስት መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በዚህም በሙስሊሙ ማህበረሰብ ስም ለመንግስት ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በመጨረሻም ለመላው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች “እንኳን ለ1 ሺህ 441ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል አደረሳችሁ” ብለዋል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.