Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ለኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የ40 ሺህ ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ለኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የ40 ሺህ ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡
የገንዘብ ድጋፍ ስምምነቱን የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የህግ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ተስፋዬ ዳባና የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር አበራ ፀጋዬ ተፈራርመዋል፡፡
ድጋፉ ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም ለሚሰጣቸውና ወደፊትም ለሚያካትታቸው አዳዲስ ስርአተ ትምህርት የዳሰሳ ጥናት በማካሄድ ክለሳ ለማድረግ የሚያስችለውን ስራ ለመደገፍ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ተስፋዬ ዳባ እንደገለፁት የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ስርአት ከማሻሻል አንፃር በፌዴራል ፖሊስ፣ በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ፣ በፍርድ ቤቶችና በፀጥታ ሃይሎች በኩል ማሻሻያዎች እየተደረጉ ነው፡፡
አሁን የተደረገው ድጋፍም በተለይም በፖሊስ በኩል ያለው ስራ በእውቀት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ከማስቻሉም በተጨማሪ የምርመራ ሂደቶች ከዘልማዳዊ አሰራር ወጥተው ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ እንዲከናወኑ ለማስቻል ከፍተኛ እገዛ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡
ምክትል ኮሚሽነር አበራ ፀጋዬ በበኩላቸው ድጋፉ ክልሎች ድረስ በመውረድና የዳሰሳ ጥናት በማድረግ ዩኒቨርሲቲው የሚሰጣቸውን ፕሮግራሞች ለመከለስ እንደሚያግዝ ገልፀው ምስጋና ማቅረባቸውን ከጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.