Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የአዳማ የኢንዱሰትሪ ፓርክን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ እና በኢትዮጵያ ጉበኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የአዳማ የኢንዱሰትሪ ፓርክን ዛሬ ጎብኝተዋል።
 
መሪዎቹ ለጉብኝቱ አዳማ ሲደርሱ የኦሮሚያ ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት ምክትል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
 
በፓርኩ በመዘዋወርም የተለያዩ የምርት ሂደቶችን እና የምርት ዓይነቶችን የተመለከቱ ሲሆን፥ ስለፓርኩም ገለፃ ተደርጎላቸዋል።
 
ከአዳማ የኢንዱስትሪ ፓርክ በተጨማሪ የገልማ አባ ገዳ አዳራሽን የጎበኙ ሲሆን፥ በዚሁ ወቅት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በጉብኝታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
 
ለመሪዎቹ የተለያዩ ስጦታዎችም ተበርክቶላቸዋል።
 
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትናንት ነበር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት።
 
የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ በተለያየ ዘርፍ ለሚሰማሩ አምራች ኩባንያዎች የሚያገለግሉ በአጠቃላይ 19 የመሥሪያ ጠለላዎች ወይም የመሥሪያ ቦታዎችን የያዘ ነው።
 
በፓርኩ ውስጥ በጨርቃ ጨርቅ፣ በማሽነሪ እና ሌሎች ቁሳቁሶች ማምረት ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች ይገኛሉ።

 

በታያየዘ ዜና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘውን የሆላንድ የእንሰሳት እርባታ እና የወተት ተዋፅኦ ማቀነባበሪያንም ጎብኝተዋል።

ማቀነባበሪያው ራሱ ከሚያረባቸው እና በአከባቢው ከሚገኙ አርሶ አደሮች ከሚሰበስበው የወተት ምርት የተለያዩ የወተት ተዋፅኦዎችን በማምረት የሚታወቅ ነው።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትናንት ነበር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት።

 
በአልአዛር ታደለ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.