Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙሃን የሰጡት ቃለ መጠይቅ በዚህ የጥሞና ወቅት እንዳይተላለፍ ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙሃን የሰጡት ቃለ መጠይቅ በዚህ የጥሞና ወቅት እንዳይተላለፍ ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን አሳሰበ።

የባለስልጣኑ  ዋና ዳይሬክተር  አቶ መሀመድ እድሪስ ለኢዜአ እንደገለጹት÷ ምንም እንኳን ቃለ መጠይቁ የመንግስት የስራ ክንውኖች  ላይ ያተኮረና የምርጫ ቅስቀሳ እንዳልሆነ ቢታወቅም በዚህ የጥሞና ወቅት ሊተላለፍ አይገባም።

የዘንድሮ ምርጫ መንግስት ከመቼውም ጊዜ በላይ ፍትሃዊ፣ ግልጽና ዴሞክራሲያዊ  እንዲሆን ቁርጠኝነቱን ያሳየበት ነው ያሉት አቶ መሀመድ ÷ ቃለ መጠይቁ ከምርጫ ጋር ግንኙነት ባይኖረውም ብዥታ እንዳይፈጠር ሲባል የመገናኛ ብዙሃኑ ከምርጫው በፊት እንዳያስተላልፉና ማስተዋወቃቸውንም እንዲያቆሙ አሳስበዋል።

በተመሳሳይ የማሕበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም የምርጫ ቅስቀሳ የሚመስሉ መልዕክቶችን በማስተላለፍ ላይ የሚገኙ አካላትም ከድርጊታቸው መታቀብ አለባቸው ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.