Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ ሚ ዐቢይ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ የሃላፊነት ጊዜያቸው ስኬታማ እንዲሆን ተመኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ፕሬዚዳንት ሆነው በመሾማቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፥ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን የሀላፊነት ጊዜያቸው ስኬታማ እና አገሪቱን ወደ ተሻለ እድገት እና ብልጽግና የሚያሻግሩበት እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡
ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸውን የሀገሪቱ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት አስታውቋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.