Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ጉብኝታቸው የኢትዮጵያውያንን መብትና ጥቅም በሚያስከብሩ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ – አቶ ንጉሱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች በሚያደርጉት ጉብኝት በሀገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን መብት እና ጥቅም የሚያስከብሩ ውይይቶችን እንደሚያደርጉ ተገለፀ።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች የሚያደርጉትን የሶስት ቀናት ጉብኝት አስመልክቶ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን መግለጫ ሰጥተዋል።
 
በመግለጫቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቆይታቸው ከ15 ሺህ ኢትዮጵያውያን ጋር ይወያያሉ ብለዋል።
 
ዜጎች ክብራቸው ተጠብቆ፣ መብታቸው ተከብሮ፣ ጥቅማቸው ተረጋግጦ እና በማንነታቸው ኮርተው እንዲኖሩ የሚያስችሉ ውይይቶችን ከዜጎች እና ከመሪዎች ጋር ያደርጋሉም ነው ያሉት።
 
አቶ ንጉሱ ዜጎች ህጋዊነትን በተላበሰ ሁኔታ እንዲሰማሩ ከማድረግ ባሻገር የህግ ስምምነቶችን ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ጋር መከናወኑን በመግለጫቸው አንስተዋል።
 
በዚህም እስካሁን ድረስ ከዮርዳኖስ፣ ኳታር፣ ሳዑዲ ዓረቢያ እና ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ጋር ስምምነት መደረሱን አስረድተዋል።
 
ስምምነቶቹ ዜጎች ያሉባቸውን ችግሮች መቅረፍ እንሚያስችሉ እና አፈፃፀማቸው ላይ ውይይት እንደሚካሄድም ነው የተናገሩት።
 
መንግስት በአሁኑ ወቅት በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ዙሪያ ትኩረት በማድረጉ እስካሁን ከ100 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን አብራርተዋል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.