Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ በወንጪ የሚገነባውን የገበታ ለሐገር ፕሮጀክት አስጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በወንጪ የሚገነባውን የገበታ ለሐገር ፕሮጄክት በዛሬው እለት በይፋ አስጀመሩ፡፡

በገበታ ለሀገር የሚለማው የወንጪ -ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም ፕሮጀክት በምዕራፎች ተከፍሎ የሚሰራ መሆኑ ተገልጿል።

የፕሮጀክቱ አስተባባሪና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ እንደተናገሩት፥ በመጀመሪያው ምዕራፍ የወንጪ እና ደንዲ ሃይቆችን የሚያገናኝ የአስፓልት መንገድ ይሰራል ብለዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ፣ የጤና ማዕከል፣ የቴሌኮም ማሻሻያ፣ በግል ባለሀብቶች የሚሰሩ መዝናኛ ስፍራዎች እንዲሁም የትምህርት ማዕከል እና አነስተኛ አውሮፕላን ማረፊያ ይገነባልም ተብሏል፡፡

የፕሮጀክቱ አስተባባሪና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ፥ ፕሮጀክቶችን መጀመርና በፍጥነት መጨረስ ልምድ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

የወንጪ – ደንዲ የተቀናጀ ኢኮ ቱሪዝም ፕሮጀክት የዲዛይንና የግንባታ ቅድመ ዝግጅት ተጠናቆ ዛሬ በይፋ ወደስራ መግባቱንም አንስተዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በተለያዩ ምዕራፎች ተከፋፍሎ እንደሚካሄድ ጠቅሰው፤ በመጀመሪያው ምዕራፍ ወደ ወንጪ ሃይቅ የሚወስደው የአስፋልት መንገድ፣ ሁለቱን ሃይቆች የሚያገናኝ የአስፋልት መንገድ፣ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት፣ የጤና ማዕከል፣ ትምህርት ቤቶች፣ የቴሌኮም ማሻሻያ ፕሮጀክት እንዲሁም በባለሃብቶች የሚገነቡ ደረጃቸውን የጠበቁ ማዕከሎችን የሚያካትት እንደሆነ ገልጸዋል።

በማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በዓላዛር ታደለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.