Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ መቀሌ በመገኘት ከከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ መቀሌ በመገኘት ከከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር መክረዋል።
በወቅቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መከላከያው ባቀደው እቅድ መሰረት ጦርነቱን አጠናቋል÷ ሰራዊቱ በህግ ማስከበሩ ሂደት ለሰራው ስራም አመስግነዋል።
ሰራዊቱ ሁሉም በአንድነትና በጀግንነት የተሰጠውን ስራም መቶ በመቶ አሳክቷል÷በተሰራው ስራ በጣም ደስተኞች ነን የኢትዮጵያ ህዝብም ኮርቶባችኋል ነው ያሉት።
ነገር ግን ወንጀለኞችን መያዝ ስራውን ባጠረ ጊዜ ጨርሰን ወደ ልማት ስራችን መሄድ ያስፈልገናል ብለዋል።
በጦርነት ተፈትነው ያሸነፉ ጀግኖች አፍርተናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጀግንነታችሁ በውጊያ ብቻ አይደለም በልማቱም እንጂ ብለዋል።
አያይዘውም ጀግና ያደርጋል እንጂ አይፎክርም ስለሆነም እንዳትፎክሩ፣ከገጠምን እናሸንፋለን እናንተ የጦር መሪዎች ይህንን በልባችሁ አኑሩ ሲሉ ተናግረዋል።
አያይዘውም ወታደር በመሆኔ በጣም ኮርቻለሁ በርቱ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.