Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድና የኤርትራው ፕሬዚዳንት የግልገል ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ግድብን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የግልገል ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ግድብን ጎበኙ፡፡

በስፍራው እየተሰራ ያለውን የ”ገበታ ለሀገር” ፕሮጀክት አካል የሆነውን የሰው ሰራሽ ሐይቅ ግንባታንም ጎብኝተዋል፡፡

በተጨማሪም በደቡብ ክልል ዳውሮ ዞን የሚገኙ የተፈጥሮ ሃብቶችንም ጎብኝተዋል፡፡

በዚህም በዳውሮ ዞን እና ኮንታ ልዩ ወረዳ እስከ ንጉስ ሃላላ ኬላ ድረስ የሚገኙ የተፈጥሮ ሃብቶችን ነው የጎበኙት፡፡

በገበታ ለሃገር ይፋ በተደረገው የኮይሻ ፕሮጀክት ዙሪያ ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ዛሬ ለሶስት ቀናት የስራ ጉብኝት ኢትዮጵያ መግባታቸው ይታወቃል፡፡

ጠዋት በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን የሚገኙ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.