Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከክልል ፕሬዚዳንቶች እና ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከክልል ፕሬዚዳንቶች እና ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በበይነ መረብ በተካሄደው በዚህ ውይይት በመጪው ምርጫ ዙሪያ ትኩረት ማድረጉ ነው የተገለጸው፡፡

በውይይቱም ክልሎች በመጪው ምርጫ ጸጥታና ሰላምን ከማስከበር፣ እንዲሁም አስፈላጊውን ግብዓት ከማሟላት አኳያ ያላቸውን ዝግጅት መገምገሙን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በትናንትናው ዕለትም ከፌደራል እና ከክልል አመራሮች ጋር በምርጫ ዙሪያ መወያየታቸው የሚታወስ ሲሆን የመንግሥት እና የፓርቲ ሥራዎች እና ኃላፊነቶች አንድ ተደርገው እንዳይቆጠሩ ግልጽ መለያዎች መቀመጣቸውም ነው የተጠቀሰው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.