Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ኢትዮጵያን በተለያዩ ሀገራት ከሚወክሉ አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያን በተለያዩ ሀገራት ከሚወክሉ አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው እንዳስታወቁት፥ “ዛሬ ከሰዓት ለሁለት ሳምንት በዘለቀው ውይይታቸው ማጠናቀቂያ ላይ ተገኝቻለሁ” ብለዋል።

በቆይታቸውም “የውጪ ፖሊሲያችንን የምናካሂድበትን ቀጣዩን ምዕራፍ በተመለከቱ ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ መክረናል” ሲሉም አስታውቀዋል።

“ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት ጋር የጠበቀ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲኖራት በማስቻል ረገድ የአምባሳደሮቻችን እና የቆንስሎቻችን ሚና የላቀ ነው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በመልእክታቸው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዋናው መስሪያ ቤት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ አምባሳደሮች እና ቆንስል ጀኔራሎች ዓመታዊ ስብሰባ ላለፉት ሁለት ሳምንታት በቢሾፍቱ ከተማ ሲካሄድ መቆየቱ ይታወሳል።

“ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኳችን ለሃገራዊ ብልጽግናችን” በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ በነበረው ውይይቱ ላይም በአዲሱ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዙሪያ እንዲሁም በኢትዮጵያ የ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ውይይት ሲያደርጉ ቆይተዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.