Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከሱዳኑ አቻቸው ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ጋር ተወያዩ፡፡
ሁለቱ መሪዎች ታሪካዊውን የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት ማጠናከር በሚያስችሉ እና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ነው ውይይት ያደረጉት፡፡
በዚሁ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ÷ የኢትዮጵያ መንግሥት በተለይም ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሱዳን እጅግ አስፈላጊ በሆነ ወቅት እንደደረሱላቸው አስታውሰዋል።
አያይዘውም ኢትዮጵያ የምታካሂደውን የሕግ ማስከበር ሥራ አስመልክቶም ሱዳን ያላትን አጋርነት ገልጸዋል።
በሁለቱ መሪዎች መካከል የተካሄደው ውይይት በበርካታ የጋራ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ ደርሰዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ዛሬ ጠዋት ነበር ለይፋዊ ስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት፡፡
በአልዓዛር ታደለ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.