Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከአማራ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አመራሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአማራ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ የክልል መስተዳድሮች ጋር መወያየታቸውን አስታወቁ፡፡

በውይይታቸው ከየክልሎቹ የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን በመተከል ዞን የተከሰቱ ግጭቶችን አስመልክቶ ውይይት ማካሄዳቸውንም በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሉትን ችግሮች በመፈተሽ የአካባቢውን ዘላቂ ሰላም ማስጠበቅ የሚያስችሉ ቀጣይ አቅጣጫዎች መቀመጣቸውንም ገልጸዋል::

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.