Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከክልል አመራሮች ጋር ለሃገራዊው ምርጫ ያለውን አጠቃላይ ዝግጅት ገመገሙ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከምርጫ ቁሳቁስ አቅርቦት፣ የምርጫ ጣቢያዎችን ከማዘጋጀት፣ ከመራጮች ምዝገባ እንዲሁም ሰላማዊ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ምርጫ እንዲከናወን የጸጥታ አካላት ካላቸው ዝግጁነት አንጻር ክልሎች ባደረጉት ቅድመ ዝግጁት ዙሪያ ተወያዩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጥር 2013 ዓ.ም. አንስቶ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር ጋር በመሆን የክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች ለምርጫ የሚያደርጉትን ቅድመ ዝግጁነት ለመገምገም እና ለሚነሱ ጉዳዮች እንደ አስፈላጊነቱ መፍትሄ ለመስጠት ስብሰባዎችን ሲያካሂዱ ቆይተዋል።

በዛሬው እለትም ከምርጫ ቁሳቁስ አቅርቦት፣ የምርጫ ጣቢያዎችን ከማዘጋጀት፣ ከመራጮች ምዝገባ እንዲሁም ሰላማዊ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ምርጫ እንዲከናወን የጸጥታ አካላት ካላቸው ዝግጁነት አንጻር እያንዳንዱ ክልል ያለውን የቅድመ ዝግጁነት ሁኔታ አሳውቋል።

ከየክልሉ የተገኘው ሪፖርት እንደሚያመላክተው በአጠቃላዩ የመራጮች ምዝገባ ቁጥር እና የምርጫ ፖሊሶችን አሰልጥኖ ዝግጁ የማድረግ ሂደቱ ጭማሪ ማሳየቱን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

የምርጫ ቦርድ መጪውን ምርጫ ለአጭር ጊዜ ማዘግየቱን አስመልክቶ፥ የክልል አመራሮች ምርጫው በቀደመው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት እንዲካሄድ ለማስቻል ያላቸውን ዝግጁነት እና ቁርጠኝነት በመጥቀስ መራዘሙ እንዳላስደሰታቸው ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.