Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ በሶማሌ ክልል የተለያዩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን በይፋ አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሶማሌ ክልል የተለያዩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን በዛሬው እለት በይፋ አስጀምረዋል።

በመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ማስጀመሪያው ላይም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተጨማሪም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የኦሮሚያ ክልል ርእስ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቅድሚያ ከጎዴ ቀላፎ ፈርፈር ሎት ያለውን የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታን ነው በይፋ ያስጀመሩት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃም “ዛሬ በሶማሌ ክልል ከ6 ቢሊየን ብር በላይ ወጭ የሚደረግባቸው እና ከ300 ኪሎ ሜትር የሚበልጥ ርዝማኔ ያላቸውን መንገዶች ግንባታ አስጀምረናል ብለዋል”።

ከእነዚህም ውስጥ ከ270 ኪሎ ሜትር በሚበልጥ ርዝማኔው የጎዴ -ቀላፎ ሎት -1 ፣ የጎዴ -ሐርጌሌ ሎት እና የያአሌ -ዳና ሎት -3 የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ያካተተ መሆኑንም አስታውቅዋል።

የመንገድ ግንባታዎቹ  በ4 ዓመታት ውስጥ የሚጠናቀቅ መሆኑንም አስታውቀዋል።

የመንገድ ግንባታው ሲጠናቀቅ የአካባቢውን ነዋሪዎች ከማገናኘት ባሻገር፣ የጎዴ ከተማን የልማት ማዕከል ለማድረና የገበያ ትስስር ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል።

በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከጅግጅጋ -ገለለሽ -ደጋሀምዶ የመንገድ ግንባታ ስራንም በዛሬው እለት በይፋ አስጀምረዋል።

መንገዱ 166 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፥ ከዚህም ውስጥ ከጅግጅጋ ገለለሽ ያለው 56 ኪሎ ሜትር ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ ቀሪው ከገለለሽ- ደጋሀመዶ- ሰገግ ያለው 110 ኪሜ ግንባታን ደግሞ ዛሬ በይፋ አስጀምረዋል።

ለግንባታው 1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ተመድቧል።

ግንባታውንም ሀገር በቀል በሆነው ቢአይካ ጀኔራል ቢዝነስ የሚገነባ መሆኑንም ኢዜአ ዘግቧል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.