Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋር ፍሎራ ቬጅ የአትክልትና ፍራፍሬ ችግኝ ማፍያን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 26 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በባቱ ከተማ የሚገኘውን ፍሎራ ቬጅ የአትክልትና ፍራፍሬ ችግኝ ማፍያን ጎበኙ።

ፍሎራ ቬጅ በዓመት 20 ሚሊየን የአትክልትና ፍራፍሬ ችግኞችን በማፍላት ለአርሶ አደሩ የሚያቀርብ ሀገር በቀል ችግኝ ማፍያ ጣቢያ ነው።

ጣቢያው በግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ትልቅ ትኩረት የተሰጠውን የመስኖ ልማት በማገዝ ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናግረዋል።

በ4 ሚሊየን ብር የተቋቋመው ይህ ተቋም ከ20 እስከ 30 ባሉት ቀናት ውስጥ የሚደርሱ የአትክልትና ፍራፍሬ ችግኞችን በማፍላት ለአርሶ አደሩ የሚያቀርብ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም ለአርሶ አደሩ የአትክልትና ፍራፍሬ ችግኝን እያፈላ እያቀረበ ያለውን ፍሎራ ቬጅን ያበረታቱ ሲሆን አቅሙን በማሳደግ አቅርቦቱን እንዲጨምር ጠይቀዋል።

በጸጋዬ ንጉስ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.