Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ወደ ስራ በመግባቱ የደስታ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ወደ ስራ በመግባቱ የደስታ መልዕክት አስተላለፉ።

አዲሱ የአፍሪካ ወሰን  አእምሮዎን ለሐሳብ፣ ገበያዎቻን ደግሞ ለንግድ ክፍት የሚሆኑበት ቀጣናዊ ውሕደት ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግድ ጥሩ ያልሆነ ግንኙነት እንደሚያስወግድ እና የተቀናጀ ገበያ ብልፅግናን  እንደሚያረጋግጥ ገልፀዋል።

በዛሬው ዕለት በይፋ ወደ ስራ የገባው የአፍሪካ የንግድ ቀጠና 1 ነጥብ 2 ቢሊየን የአህጉሪቱን ህዝቦች ገበያ እና 3 ቢሊየን ዶላር የሚገመተውን የሀገር ውስጥ ምርት የያዘ ነው።

በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት ላይ ከኤርትራ በስተቀር 54ቱ የአፍሪካ ሀገራት ፊርማቸውን አስቀምጠዋል።

ስምምነቱ በአህጉሪቱ በሚገኙ ሀገራት መከካል ንግድ ያሳልጣል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ሲሆን ለምርት እና አገልግሎቶች ነጠላ ገበያ ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

አፍሪካ በታሪኳ ዝቅተኛው አህጉራዊ የንግድ ትስስር ያላት ሲሆን በፈረንጆቹ 2017 የአፍሪካ ሀገራት እርስ በርስ የነበራቸው የንግድ ልውጥጥ በመቶኛ 16 ነጥብ 6 ብቻ ነበር።

ይህም 68 በመቶ በአውሮፓ እና 59 በመቶ ከሆነው የእስያ ገበያ ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ መሆኑ ተነግሯል።

በዛሬው ዕለት ወደ ስራ የገባው የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና በሀገራቱ መካከል ያለውን ንግድ 50 በመቶ ያሳድገዋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.