Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ያቀረቡት ጥሪ የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ ድጋሚ እንዲያብብ ይረዳል–ረ/ፕሮፌሰር አህመድ ዘካሪያ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለጥቁር ሕዝቦች ያቀረቡት ጥሪ የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ ድጋሚ እንዲያብብ ይረዳል ሲሉ የታሪክ መምህርና የአገር ሽማግሌ የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር አህመድ ዘካሪያ ተናገሩ፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለጥቁር የአፍሪካ ሕዝቦች ያስተላለፉት ጥሪ ተቀዛቅዞ የነበረው የፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ ዳግም እንዲጀምር ከማድረግ አንፃር የራሱ የሆነ በጎ ተጽዕኖ እንዳለው ረዳት ፕሮፌሰሩ ገልጸዋል፡፡
 
ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 1960ዎቹ ብዙ የአፍሪካ አገሮች ከቅኝ አገዛዝ ነፃ መውጣት የመሠረት ድንጋይ የጣለችና በቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በአሁኑ የአፍሪካ ሕብረት በኩል ስለ አፍሪካ ብዙ የተሟገተች አገር መሆኗን አውስተዋል፡፡
 
በዚህም በርካታ የአፍሪካ አገሮች የነፃነት ተምሳሌትና እናት አድርገው እንደሚመለከቷት ከኢፕድ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል፡፡
 
ጥሪው ምዕራባውያን ዳግም እያመጡብን ያለውን የባርነት ቀንበር በጋራ እንስበር ከሚል የመነጨ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች በመልካም እየተቀበሉትና በጎ ምላሽ እየሰጡት መሆኑ እየታየ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.