Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ፕሮፌሰር ሂሩት ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት በእጩነት በመቅረባቸው ድጋፋቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት በእጩነት በመቅረባቸው ድጋፋቸውን ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ፕሮፌሰር ሂሩት ለቦታው ትክከለኛ ዕጩ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ፕሮፌሰር ሂሩት የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን አሁን ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሆነው እያገለገሉ ይገኛል፡፡

ፕሮፌሰር ሂሩት ለህብረቱ የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት ከሳምንት በፊት መቅረባቸው ይታወሳል፡፡

በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት ፕሮፌሰር ሂሩት ኢትዮጵያን በመወከል ነው ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት በእጩነት የቀረቡት፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.