Fana: At a Speed of Life!

ጣሊያን የአውሮፓ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነች

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ትላንት ምሽት በተካሄደው የ2020 የአውሮፓ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ጣልያን ሻምፒዮን ሆናለች፡፡
በዌምብሌይ ስታዲየም በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ጣሊያን እንግሊዝን በፍጽም ቅጣት ምት በማሸነፍ ነው ሻምፒዮን የሆነችው፡፡
ጨዋታው በተጀመረ 2ኛው ደቂቃ ላይ ሉክ ሻው እንግሊዝን ቀዳሚ ያደረገችውን ግብ አስቆጥሯል፡፡
ይሁን እንጂ 67ኛው ደቂቃ ላይ ሊዮናርዶ ቦኑቺ ጣልያንን አቻ የሚያደርጋትን ግብ ማስቆጠሩን ተከትሎ ጨዋታው 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡
መደበኛ ጨዋታው በአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ በተሰጠ የመለያ ምትም ጣሊያን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸፍ የ2020 የአውሮፓ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆናለች፡፡
ምንጭ ÷ ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.