Fana: At a Speed of Life!

ጣሊያን የአፍሪካ ሕብረት-መር የህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድርን እንደምትደግፍ ገለፀች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ ዓለም በናይሮቢ ከጣሊያን አምባሳደር አልቤርቶ ፔይሪ ጋር በሁለትዮሽ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
አምባሳደር ፔይሪ ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር ስትራቴጂያዊ ትብብር እንዳላት እንዲሁም ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት አስፈላጊ አገር እንደሆነች ተናግረዋል።
አምባሳደር ፔይሪ የህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር በአፍሪካ ሕብረት በተያዘው መሠረት እንዲቀጥል አገራቸው እንደምትደግፍ መግለፃቸውን በናይሮቢ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.