Fana: At a Speed of Life!

ጥሩነሽ ዲባባ ባለፉት 75 ዓመት ከታዩት ሴት አትሌቶች ታላቋ ተብላ በአትሌቲክስ ዊክሊ አንባቢያን ተመረጠች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያዊቷ ጥሩነሽ ዲባባ እና ጀማይካዊው ዩዜን ቦልት ባለፉት 75 ዓመት ከታዩት ሴት እና ወንድ አትሌቶች መካከል ታላቆቹ ተብለው በአትሌቲክስ ዊክሊ አንባቢያን ተመረጡ።
75ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ የሚገኘው አትሌቲክስ ዊክሊ ለአንባቢያኑ ”ለእናንተ ታላላቅ አትሌቶች እነማን ናቸው?” የሚል ጥያቄን አንስቷል።
በዚህም የመፅሄቱ አንባቢያን በአትሌቲክስ ዘርፍ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባን በሴቶች እና ዩዜን ቦልትን በወንዶች ታላላቅ አትሌቶች ብለው መርጠዋቸዋል።
በአንባቢያኑ አትሌት ጥሩነሽ 31 ነጥብ 1 በመቶ በማግኘት ቀዳሚ ስትሆን፤ ዩዜን ቦልት ደግሞ 55 ነጥብ 3 በመቶ ማግኘት በወንዶቹ ቀዳሚ ሆኗል።
አንጋፈው አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴም 17 ነጥብ 1 በመቶ በማግኘት በወንዶቹ ሁለተኛው ታላቅ አትሌት በመሆን በአንባቢያኑ ተመርጧል።

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.