Fana: At a Speed of Life!

ጽንፈኝነትና አክራሪነት እያስከተለ ያለውን ጥፋት ለመግታት መንግስት በድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በዋናነት ብሔር እና ሃይማኖትን ሸፋን ያደረገ ጽንፈኝነትና አክራሪነት እያስከተለ ያለውን ጥፋት ለመግታት መንግስት በድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ጌታሰው እንዳለው እንደገለጹት ÷ አሁን ላይ ብሔር እና ሃይማኖትን ሽፋን ያደረገ ጽንፈኝነት የሚፈጥረው ችግር እየተባባሰ መጥቷል።

ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ፣ በጽንፈኛ በብሔር እና በሃይማኖት “አቀንቃኝ” ጽንፈሾች አነሳሽነትና ቆስቋሽነት ንጹሃን ዜጎችን ሰለባ ያደረጉ በርካታ ጥቃቶች እየተፈጸሙ መሆናቸውን ገልጸው፥ ከጀርባቸው ሀገርና ህዝብን ለዘለቄታው የማዳከም ዓላማ የያዙ አካላት መኖራቸውም አያጠያይቅም ብለዋል፡፡

የፖሊቲካ ሳይንስ መምህሩ እንደሚሉት፥ በብሔር ማንነት እና በሃይማኖት ልዩነት ሰበብ ሌላውን ጎድቼ ፍላጎቴን አሳካለሁ በማለት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ማንንም ተጠቃሚ አንደማያደርጉም ሊታወቅ ይገባል።

ከሰሞኑ መመልከት እንደተቻለው ቦታ እየቀያየረ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚታየው ስርዓት አልበኝነት የዜጎችን ደህንነት አደጋ ላይ መጣሉ አጠያያቂ ባለመሆኑ፥ መንግስት ዋነኛ ኃላፊነቱ የሆነውን የዜጎችን ደህንነት የማረጋገጥ ስራ ላይ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባው ጠቁመዋል።

በዚህ ውስጥ የሁሉም ዜጋ ግዴታን በማወቅና መብትን በማስከበር ሂደት ኃላፊነቱን በብቃት መወጣት እንደሚገባውም ነው ያመላከቱት።

የተለያዩ አካላት ፍላጎቶች ሊሳኩ የሚችሉት በጋራ ምክክርና መግባባት እንጂ ብቸኛ ትርፉ ውድመት በሆነ ግጭት አለመሆኑን በማመን፣ በአብሮነት የጋራ ደህንነትንና ሰላምን ማስጠበቅ ይገባልም ነው ያሉት።

በበርናባስ ተስፋዬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.