Fana: At a Speed of Life!

ፈረንሳይ አካባቢ በተደረገ ፍተሻ በርካታ አደንዛዥ ዕፅ፣ መሳሪያዎችና ሌሎችም ቁሶች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በየካ ክ/ከተማ የፈረንሳይ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ባደረገው ፍተሻ በርካታ አደንዛዥ ዕፅና የአሸባሪውን መልዕክት የያዙ በራሪ ወረቀቶች፤ ቲሽርቶች እና የጦር መሳሪዎች እንዲሁም በርከት ያሉ የጸጥታ ሃይል አልባሳት መያዙን ገለጸ።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መሰረት ባደረገ ፍተሻና ብርበራ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተለያዩ ውጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛል፡፡
በየካ ክ/ከተማ የፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በአራቱ ወረዳዎች ውስጥ በ15 ቤቶች ላይ በተደረገ ፍተሻ አንድ ሳጥን ሐሺሽ፣ ለሽብር ተግባር ቀስቃሽ የሆኑ በራሪ ወረቀቶች፣ የሽብርተኛው የትህነግን ተግባርን የሚያስተጋቡ ቲሸርቶ፣ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ፤የተለያዩ የጸጥታ ሃይሎች አልባሳት እና መድኃኒቶች መያዙን የፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ፍቃዱ ጽጌ ገልፀዋል።
የፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ ፖሊስ ከህብረተሰቡ በሚደረስ ጥቆማና መረጃ መሰረት ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመሆን በተደረገ ፍተሻ በአንድ ግለሰብ ቤት ላይ ብቻ በርከት ያሉ የታሸገ እና የተተከለ ካናቢስ የተባለ አደንዛዥ ዕፅ የተያዘ ሲሆን ፥ግለሰቡም እንደሚጠቀምና እንደሚያከፋፍል ዋና ኢ/ር ፍቃዱ ጽጌ ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም የተለያዩ አይነት የጦር መሳሪዎች ቦንብን ጨምሮ በፍተሻው እንደተያዙ ዋና ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል።
ህብረተሰቡ ሃገርን ለማዳን የአሽባሪዎችን ስራ ለማጋለጥ እያደረገ ያለው ጥረት ውጤታማ መሆኑን በመግለፅ ህብረተሰቡ ለፖሊስ እየሰጠ ላለው ተጨባጭ መረጃ ኃላፊው ምስጋናማቅረባቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
0
People reached
2
Engagements
Boost post
2
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.