Fana: At a Speed of Life!

በፈረንጆች 2022 የዓለም ኢኮኖሚ 100 ትሪሊየን ዶላር እንደሚያልፍ ጥናት አመለከተ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአለም ኢኮኖሚ በፈረንጆች 2022 ለመጀመሪያ ጊዜ 100 ትሪሊየን የአሜሪካ ዶላርን እንደሚያልፍ በብሪታንያ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ጥናት ማዕከል ያወጣው ጥናት አመለከተ፡፡
በማዕከሉ ጥናት ውጤቱ ላይ የተቀመጠው የዓለም ኢኮኖሚ ሊግ ሠንጠረዥ 2022 ትንበያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ግምት ጋር የሚስማማ ሲሆን፥ የአለም ጠቅላላ ምርት በዶላር እና አሁን ባለው ዋጋ ከ100 ትሪሊየን ዶላር እንደሚያልፍ ተንብይዋል፡፡
በፈረንጆች 2021 የተመዘገበው የዓለም ኢኮኖሚ እድገት 5 ነጥብ 5 በመቶ የነበረ ሲሆን፥ ከአመት በፊት ከነበረው የ5 ነጥብ 3 በመቶ ትንሽ ብልጫ እንዳለው ዘገባው ይጠቅሳል።
ድርጅቱ በሪፖርቱ እንደገለጸው በ2021 ሁለተኛ አጋማሽ ላይ የሸቀጦች እና ያለቀላቸው እቃዎች እጥረትና የማጓጓዣ ችግር እና መሰል ተግዳሮቶች የዋጋ ግሽበት እንዲፈጠር አድርገዋል፡፡
የማዕከሉ ምክትል ስራ አስኪያጅ ዳግላስ ማክዊሊያምስ የ2020ዎቹ አብይ ትኩረት የሚሆነው የዓለም ኢኮኖሚ የዋጋ ግሽበትን እንዴት ይቋቋማል የሚለው ይሆናል ብለዋል፡፡
በአንጻራዊ ሁኔታ መጠነኛ ማስተካከያ በማድረግ የዋጋ ግሽበትን መቋቋም እንደሚቻል በመጠቆም፥ ያን ማድረግ ካልተቻለ ግን በ2023 ወይም 2024 የዓለም ኢኮኖሚ ወደታች መንሸራተት ሊያጋጥመው ይችላል ማለታቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.